top of page

About

ጸሐፊዋ ታደለች ኃ/ሚካኤል ለትምህርት በቆዩበት ስዊዘርላንድ፣ ዲሞክራሲ፣ ፍትህና እኩልነት በአገር ውስጥ እንዲሰፍን ከሚታገሉት የኢሕአፓ እንቅስቃሴ መሪዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት ፈጥረዋል። ይህም ወዳላሰቡት የፖለቲካ አለም አስገብቷቸዋል።

 

በአውሮፓ ስዊዘርላንድና በአገር ውስጥ ተሳትፏቸውን አጎልብተው፣ በመርሃቤቴና በመንዝ የትጥቅ ትግል እስከመመሥረት ተጉዘዋል። የኢህአፓ መሥራች የሆነው ባለቤታችውና የሦስት ሴት ልጆቻቸው አባት ብርሃነ መስቀል ረዳን ለሞት የዳረገው የትግል እንቅስቃሴ እሳቸውን ከ12 ዓመታት በላይ በእስር እንዲቆዩ ምክንያት ሆኗል።

 

ከእስር ከተፈቱም በኋላ የመጀመሪያዋ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስቴር በመሆን ለ11 ዓመታት እንዲሁም በባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት በኮትዲቯር እና በፈረንሳይ ለ8 ዓመታት አገልግለዋል።

bottom of page