ዳኛው ማነው?
ለ አመታት በጉጉት የተጠበቀው መፅሀፍዋ በቅርቡ በገበያ ላይ የውላል:: መፅሀፉን ቀድመው ለማዘዝ እና ስለ ሚድያ ዝግጅቶቻችን ለመስማት ስምና አድራሻዎን በዚህ ያስፍሩ፡፡
Tadelech's highly anticipated memoir will be available for purchase soon. To order your copy and to be notified about events related to the release please subscribe below.
Tadelech's memoir about her and Berhanemeskel's life and struggle in the Ethiopian Students Movement and EPRP
"ለኢትዮጲያ አዲሱ ትውልድ እና ስለዓለም ሕዝባዊ ትግሎች ጥናት ለሚያደርጉ ተማሪዎች እጅግ ጠቃሚ ንባብ ነው። እህታችን ታደለች የሰጠችው ሀቀኛ፣ ሚዛናዊ እና ልባዊ ምስክርነት ለሁላችንም ባለውለታ መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው።"
የፍልስፍና እና የህግ ፕሮፌሰር
እንድርያስ እሸቴ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
"በድብቅ ይካሄድ የነበረው የብርሃነ መስቀልና ታደለች የፍቅር ሕይወት ሦስት ልጆችን አፍርቷል። እነሆ አሁን ደግሞ አራተኛ ልጃቸው በዚህ መጽሐፍ መልክ ተከስቷል። ዘግይቶ የመጣ ቢሆንም የፍቅርና የትግል ሕይወታቸውን ሙሉ ስዕል ለማግኘት በእጅጉ ይረዳል። ስለሆነም በዘመኑ ከተጻፉ ትውስቶች መካከል ቁንጮ ሥፍራ ሊይዝ የሚገባው ትርክት እንደሚሆን አያጠራጥርም።"
የታሪክ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
"ብርሃነ መስቀል በዳይ ወይንስ ተበዳይ? የዛን ትውልድ ውስብስብ ታሪክ አንድ ገጽታ ይዛልን አምባሳደር ታደለች ቀርባለች። በዳኛው ማነው? የዛን ትውልድ መስዋዕትነት በተለመደ ግልጽነቷና ሰብዓዊነት በተላበሰ አቀራረብ በጥሩ ቋንቋ ገልፃዋለች።"
ልዑል በዕደማርያም መኮንን
ኢትዮጵያ
"የታዲ ውብ የፍቅርና ሰፊ የፖለቲካ ትርክት ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገር በአላማ መፅናት እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ድረስ ሊያስከፍል መቻሉን ያሳያል ትምህርት ሰጪ እንደሚሆንም ተስፋ አደርጋለው።"
ወ/ሮ እንጉዳይ በቀለ - ፀሃፊ
"ከባህር ዛፉ ጥላዎች ስር"
Reviews
ስለ መጽሃፉ የተሰጡ አስተያየቶች
For media inquiries,
please contact H.B. Redda at
+251 94 431 7700
Addis Ababa